ልማቱ የመዲናች አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ ገፅታ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

ልማቱ የመዲናች አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ ገፅታ የቀየረና የአፍሪካ ተምሳሌት መሆኗን ያረጋገጠ መሆኑ ተገለጸ።

የጉብኝቱ ተሳታፊ ነጋዴዎች በጉብኝታቸው ወቅት የተመለከቷቸው የልማት ስራዎች አስገራሚ ፣ አስደናቂና በአጭር ጊዜ የተሰራ መሆኑን ለማመን የሚከብድና የአመራሩ ቁርጠኝነትና ትጋት ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

 

ባለፉት አጭር የለውጥ አመታት አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብና አዲስ ፣ የቱሪስት መዳረሻ ፣ የትውልድ ግንባታ ማዕከል ፣ የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በርካታ የልማት ስራ መሰራቱን መመልከታቸውን ገልፀው የተሰሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል እና ለትውልድ የማሸጋገር ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል።

 

መንግስት የገባውን ቃል ወደ ተግባር የለወጠበት መሆኑን የተሰሩት የልማት ስራዎች ማሳያ ናቸው ያሉት ነጋዴዎቹ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ በመሆኑ በልማቱ ላይ ያላቸውን ሁለንተናዊ ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

 

ልማቱን እያስጎበኙ ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ የኢንደስትሪ ልማት ቢሮ የአምራች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ ኩሳ እንደተናገሩት የተሰሩ ልማቶች የዜጎችን ህይወት ወደ ተሻለ ምዕሪፍ ያሸጋገረና የከተማችንን ከፍታ በማረጋገጥ ከእህት ከተሞች ተወዳዳሪና የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ዕውቅና ያስገኘ መሆኑን አብራርተው በዚህም የንግዱ ማህበረሰብ ሚና የጎላ እንደነበርና በቀጣይ በተጠናከረ መንገድ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

 

አቶ በላይነህ ሙሉጌታ የአራዳ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ በበኩላቸው መንግስት ለዜጎቹ የገባውን ቃል በተግባር ያሳየበትና የንግዱ ማህበረሰብም በባለቤትነት የተሳተፈበት የጋራ የልማት ውጤት እንደሆነ ገልፀዋል። አክለውም የንግዱ ማህበረሰብ ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት መሰረት ነው ብለው መንግስት እየሰራ በሚገኘው የልማት ስራ ውስጥ የዜጎች ፍትሀዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

 

አምራች ዜጋን የማፍራትና በልማቱ ተሳታፊ የማድረግ ስራ ለውጤት አብቅቶናል ያሉት የክ/ከተማው የኢንደስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሽኩሪያ መሀመድ አምራች ኢንደስትሪዎች በልማቱ ያበረከቱት አስተዋፅኦ የሚበረታታ ሲሆን በቀጣይም መንግስት ባመቻቸላቸው ዕድል በመጠቀም ጥራት ያላቸው ምርቶች በማቅረብ የሀገር ኢኮኖሚ ላይ ያላቸውን ጉልህ ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments