ከከተማችን የተለያዩ የንግድና የዘርፍ ማህበራት...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

ከከተማችን የተለያዩ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ከተውጣጡ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይተናል።

በየደረጃው ከንግዱ ማህበረሰቡ ጋር ሲካሄድ የቆየው 4ኛ እና የማጠቃለያ መድረክ በሆነው በዚህ ውይይት ከተማችንን እንደ ስሟ ውብ እና አዲስ እያደረጉ ያሉ በርካታ የልማት ስራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለነዋሪዎቻችን ግልጋሎት ክፍት እንድናደርግ፤ ህፃናት ተመግበዉ፣ ተመሳሳይ ዩኒፎርም ለብሰው እና የትምህርት ቁሳቁስ ተሟልቶላቸው እንዲማሩ ያገዙንን ግብር ከፋዮቻችንን አመስግነናል።

 

የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች በፍትሃዊ የንግድ ስርዓት እና ዘመናዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓት ዝርጋታ፣ የአሰራር ስርዓት በማዘመን፣ በአንዳንድ ፈፃሚዎቻቻንም ሆነ ነጋዴዎች ዘንድ የሚታዩ የስነ ምግባር ጉድለቶችን ማረም እንዲሁም የፈፃሚዎችን አቅም በማሳደግ ረገድ የተጀመሩ ስራዎችን ይበልጥ ለማላቅ በቅርበት አብረን ለመስራት ተግባብተናል።

 

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments