የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ፅ...

image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ፅህፈት ቤት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርት ማሳያና የልምድ ልውውጥ ማዕከል ተግባራዊ አደረገ።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት እንዲሁም እርስ በርስ ልምድ የሚለዋወጡበት ማዕከል ማቋቋሙን አስታወቀ።

 

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ የኔው ሞሴ ይህ ማዕከል ለአምራቾች የገበያ ዕድሎችን ከማስፋት ባለፈ የተለያዩ ምርቶችና ቴክኖሎጂዎች የሚተዋወቁበት እንደሚሆን ገልጸዋል።

 

በማዕከሉ ውስጥ ኤክስፖርት የሚደረጉ ምርቶች፣ ተተኪ ምርቶች፣ የቡናና የባልትና ውጤቶች፣ የህፃናት ቦርሳዎች፣ አልባሳት፣ የተለያዩ ቅባቶችና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች እንደሚገኙ የገለፁት አቶ የኔው በተለይም ለኮሪደር ልማት እየዋሉ ያሉ የእግረኛ መንገድ ንጣፎች ከሚቀርቡት ውጤቶች መካከል ተጠቃሽ እንደሆኑም አመላክተዋል።

 

ይህ ማዕከል በአምራቾች መካከል ያለውን የገበያ ሰንሰለት በማጠናከር ለኢንዱስትሪዎች እድገት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግም አቶ የኔው አክለዋል።

 


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments