አምራች ኢንዱስትሪው በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ድር...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

አምራች ኢንዱስትሪው በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ድርሻውን ከፍ ለመድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ

በ2017 በጀት ዓመት ቢሮው ከእቅድ አንጻር የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡን የተከበሩ አቶ ጃንጥራር ገለጹ፡፡

በሚቀጥለው በጀት ዓመት የአምራች ኢንዱስትሪዎች ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ፣ ችግራቸውን ለመፍታት የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማጥናት እንደሚሰራ መክትል ከንቲባ አቶ ጃጥራር አባይ ገልጸዋል።

ምክትል ከንቲባው አክለውም ለአምራች ኢንዱስትሪዎች በሚደረገው ድጋፍ ለሚያነሱት የመስሪያ ቦታ ጥያቄ ከተማዋ ካላት አቅም አንጻር በማየት ግልጽ በሆነ መልኩ ምላሽ ሲሰጥ ቆይቷል:: ወደፊትም እየተመዘነና የቅድሚያ ቅድሚያ ሊወሰንላቸው የሚችሉትን የመለየት ስራ ይሰራል ብለዋል::

በበጀት ዓመቱ የተስተዋሉ ህጸጾችን ማስተካከል፣ አምራች ኢንዱስትሪዎች የስራ እድል እንዲፈጥሩ ግንዛቤ መፍጠር፣ ለባለሙያው ሙያዊ ስልጠና መስጠት እንዲሁም የሰው ሀይል ማሟላት በቀጣይ በጀት ዓመት ትኩረት ተሰጥተው እንዲሰሩ የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ አሳስበዋል ።

በመጨረሻም ከማእከል እስከ ክፍለ ከተማ ያሉ የዘርፉ አመራሮች ሰራተኞች ዘርፉ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ያለውን ሚና በመረዳት በርብርብ ሰርተው ላስመዘገቡት ውጤት ምስጋና አቅርበዋል።

 በበጀት ዓመቱ እቅድ አፈጻጸም መሰረት ባደረገው ምዘና የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ባለሙያዎች፣ ቡድን መሪ፣ ዳይሬክተር እንዲሁም ክፍለ ከተሞች እውቅና ተሰጥቷል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments