"የኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

"የኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን ማሳደግ አስፈላጊ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

የኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊ እንደሆነ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ፡፡

ቢሮው በ2018 በጀት ዓመት ከባለድርሻ አካላት ተቋማት ጋር በቅንጅት ለመስራት የስምምነት ሰነድ (MOU) ፊርማ ስነ-ስርዓት በዛሬው እለት አካሂዷል፡፡

ያለ ኢንዱስትሪ ልማት ያደገ እና የተለወጠ የሀገር ኢኮኖሚ የለም ያሉት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ባለድርሻ አካላት አምራቾች ለሀገር ኢኮኖሚ ያላቸውን አስተዋጽኦ በመረዳት የራሳቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡

አቶ ጃንጥራር አክለውም ተኪምርት በማምረት የሀገር ውስጥ የተኪምርት ሽፋንን ለማሳደግ ፣ከውጭ የሚገዙ ምርቶችን መቀነስ እና ወደውጭ የሚላኩ ምርቶችን ለመጨመር በቅንጅት መስራቱ ይበልጥ ውጤታማ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም በከተማችን አዲስ አበባ የሚገኙ አነስተኛ፣መካከለኛ እና ከፍተኛ አምራች ኢንዲስትሪዎችን የፋይናንስ፣ የካፒታል ሊዝ ፋይናንስ፣ የመሰረተ ልማት ግብይት እንዲሁም የሰለጠነ ባለሙያ ስለሚያስፈልጋቸው ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በተያዘው 2018 በጀት ዓመትም በቅንጅት የተሻለ ስራ ለመስራት በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቶ ጃንጥራር አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት በነበረው ቅንጅታዊ አሰራር የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው ባለድርሻ አካላት እውቅናና ሽልማት አበርክቷል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments