አዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች በ7ኛው አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄዱ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ኢትዮጵያን ለማልበስ በመትከል ማንሰራራት በሚል ቃል እየተከናወነ ያለውን የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ለማሳካት ህብረተሰቡ በስፋት እየተሳተፈ እንደሆነ ገልጸዋል።
ከተማ አስተዳደራችንም በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ ፕሮግራምን በሁሉም ወረዳዎች እያካሄደ እንደሆነ አቶ ጃንጥራር ገልጸዋል።
በሀገር ዓቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል ፕሮግራም እየተከናወነ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ይተከላሉ፡፡
ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር በተገኙበት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በዛሬው እለት በአንድ ጀንበር ከ15 ሽህ በላይ ችግኞች እንደሚተከሉ የተገለጸ ሲሆን አመራሮች፣ የመግስት ሰራተኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የጸጥታ አካላት፣ ህፃናት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እየተሳተፉ ይገኛሉ።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments