




በእሁድ ገበያ የሚቀርቡ የፍጆታ ምርቶች ገበያውን የማረጋጋት ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን ሸማቾች ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ያለውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት የገበያ ማረጋጋት የንግድ ቁጥጥርና አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ታምርት ግብረ ሀይል በማቋቋም እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።
ግብረ ሀይሉ የ90 ቀናት እቅድ በማቀድ በገበያው ውስጥ የግብርና ምርት አቅርቦትን በማስፋት፣ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ከፋብሪካ በቀጥታ ለሸማቹ በማቅረብ፣ ማህበራትና ዩኒዮኖችን እንዲሁም በንግድ ስራዎች ምርቶቻቸውን በተመረጡ የእሁድ ገበያ በማቅረብ አምራቹንና ሸማቹን በማገናኘት በትኩረት እየሰራ ይገኛል::
በዛሬው እለትም በተለያዩ ክ/ከተሞች ተዘዋውረን ባየንባቸው በእሁድ ገበያ የቀረቡት የፍጆታ ምርቶች በጥራትና በአቅርቦት ተመራጭ መሆኑን እና ከነፃ ገበያው ጋር ሲነፃፀርም የዋጋ ቅናሽ እንዳለው ያነጋገርናቸው ሸማቾች ገልጸዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments