ቢሮው አመራሮችና ሠራተኞች በጋራ የወርቃማ ሰኞን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- ውስጥ Uncategorized    0

ቢሮው አመራሮችና ሠራተኞች በጋራ የወርቃማ ሰኞን የአብሮነት መማማሪያ እና የእውቀት ሽግግር ውይይት አድርገዋል ፡፡

የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የወርቃማ ሰኞ አብሮነት መማማሪያ እና የእውቀት ሽግግር ቀን በዛሬው ዕለት ከቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች ጋር “የቡድን ሥራ ለተቋማዊ ውጤታማነት” ርዕስ ላይ ውይይት ተደርጓል።

 

‎በዕለቱም በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የፋሲሊቴሽንና የካይዘን ትግበራ ዘርፍ ኃላፊ ኤፍሬም ግዛው (ዶ/ር) “የቡድን ሥራ ለተቋማዊ ውጤታማነት” በሚል ርዕስ የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል፡፡

ተባባብሮ የመስራት ውጤታማነት ለቋማት ያለውን ጠቀሜታ የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች የተቋሙን ራዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴቶችን አውቆና ተገንዝቦ መስራት ውጤታማ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

 

ዶ/ር ኤፍሬም አክለውም አንድን ተቋም ወይም ድርጅት ስኬታማ የሚያደርጉት ከአመለካከት እና ከአስተሳሰብ በተጨማሪ በተቋማት ግብ ላይ የተመሠረተ የጋራ የቡድን ሥራ ሲኖር እና ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም በዕቅድ የሚመራ የጋራ የቡድን ስብስብ ሲኖር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ግልፀኝነት እና መደማመጥ ለቡድን ሥራ እና ለተቋማዊ ውጤታማነት ከፍተኛ የሆነ ድርሻ እንዳለው እንደቢሮ ስኬታማ የሆንባቸው ሥራዎች ማሳያ ናቸው ሲሉ ዶ/ር ኤፍሬም ተናግረዋል፡፡

 

‎የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች በጋራ የሚማማሩበት የሠራተኛውን አብሮ የመስራት መንፈስ የሚያጠናክር ተግባቦትን የሚፈጥሩበት እና የቡድን ሥራ ባህልን የሚፈጥር እንደሆነ አስተያየት


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.