






ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት የነበሩ ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠልና ክፍተቶችን በማስተካከል በ2018 የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ከዘርፉ አመራር፣ ዳይሬክተርና አስተባባሪዎች ጋር ተወያይቷል።
ውይይቱን የመሩት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የፋሲሊቴሽንና የካይዘን ትግበራ ዘርፍ ኃላፊ ኤፍሬም ግዛው (ዶ/ር) ቴክኒካል ድጋፍ በማድረግ በበጀት ዓመቱ ካይዘን የተገበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲጨምሩ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ የዝግጅት ምዕራፍ ላይ የመሠረተ ልማት ችግርን በመፍታት የግብዓት አቅርቦትና የገቢያ ትስስር በማድረግ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመናበብ ለ2018 በጀት ዓመት ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ማድረግ እንደሚገባ ዶ/ር ኤፍሬም ገልጸዋል።
በመጨረሻም ምርትና ምርታማነት ውጤታማ እንዲሆንና የማምረት አቅም ልኬት እንዲጨምር የ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር በቅንጅት በመስራት እንደሚገባ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአምራች ኢንዱስትሪ ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ ኩሳ አሳስበዋል።
ቢሮው በ2017 በጀት አመት በኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው ምዘና አንደኛ በመውጣት ሽልማቶችን እና በከተማ ደረጃ ደግሞ አረንጓዴ ውስጥ መግባት ከቻሉ ተቋማት ውስጥ አንዱ በመሆን እውቅናና ሽልማት ማግኘቱ ይታወቃል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments