በመዲናዋ በተኪ ምርት ላይ ለሚሰማሩ አልሚዎች አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተኪ ምርቶች ላይ ለሚሰማሩ አልሚዎች አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
ከንቲባ አዳነችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች የአቃቂ ቃሊቲ የኢንዱስትሪ መንደርን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም የተሽከርካሪ መለዋወጫ ማምረቻዎችን፣ የቀለም ፋብሪካዎችን፣ የመኖ ማቀነባበሪያዎችን፣ የፍሪጅ መገጣጠሚያዎችንና የጨርቃ ጨርቅ ማምረቻዎችን ተመልክተዋል፡፡
በተጨማሪም የካልሺዬም ካርቦኔት ማምረቻን፣ የጫማ ክር ማምረቻዎችን፣ የግንባታ ግብዓት ማምረቻዎችንና የመስሪያ ቦታ ሼዶችን ጎብኝተዋል፡፡
ከንቲባዋ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የጉብኝት መርሐ ግብሩ የኢንዱስትሪ መንደሮችን ለመደገፍ እና ግብዓት ለማቅረብ ያለመ ነው፡፡
በኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርቶች እየተመረቱ መሆኑን ጠቁመው ÷ ይህም የውጭ ምንዛሪ ችግርን እንደሚፈታ አመልክተዋል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ በተኪ ምርቶች ላይ ለሚሰማሩ አልሚዎች አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments