የአዲሰ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክተል ከንቲባ እና የኢንዱሰትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ አምራች ኢንዱስትሪው ያለባቸውን ችግር በመለየት ለመፍታት እና በቀጣይ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ጥናት ለማስጠናት ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር ተፈራርመዋል።
ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አምራች ኢንዱስትሪው እንደ ሀገር ልዩ ትኩረት ከተሰጠው ዘርፍ አንዱ እንደሆነ ገልጸው ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮም ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
ይህ ጥናት ኢንዱስትሪው ያለበትን ችግር በመለየት ለመፍታት፣ኢንዱስትሪው ያመጣውን ለውጥ ለመለየት እና በቀጣይስ አምራቾች ምን ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል የሚለውን በመለየት የዘርፉን እድገት ለማሳደግ ወሳኝ እንደሆነ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ገልጸዋል፡፡
የአምራቾችን ምርታማነት ለማሳደግ የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ሊንኬጅ በሚል በጋራ እየሰሩ እንደሆነ የገለጹት ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ተቋማት ከመሆን ባሻገር ኢንዱስትሪዎችን ለማሳደግ የሚጠበቅባቸውን ስራ መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡
ጥናቱን የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለማሳደግ በከተማ አስተዳደሩም ሆነ በቢሮው ምን መደረግ አለበት የሚለውን ለመለየት ወሳኝ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደረጀ እንግዳ በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲው ዓላማ የኢንዱስትሪዎችን አቅም ማጉልበትና ተወዳዳሪ ለማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ደረጀ እንግዳ አክለዉም ጥናቱን በተያዘለት ጊዜ በጥራት ተጠናቆ አላማውን እንዲያሳካ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ከጥናት ቡድኑ ጋር በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments