ኢንዱስትሪዎች ከባንኮች ጋር ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ ።
ቢሮው ከሀያ ሶስት በላይ ከሆኑ የሚመለከታቸው የባንክ ሀላፊዎች፣ ከ150 በላይ ብድር ጥያቄ ያላቸው ኢንዱስትሪዎችና የሚመለከታቸው ተቋማት በተገኙበት ውይይት አካሄደ።
የከተማ አስተዳደሩ የአምራች ኢንዱስትሪውን ሂደት ለማሳለጥና ባለሀብቶች የሚገጥሟቸውን የብድርና የሊዝ አቅርቦት ችግሮች ለመፍታት ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ገልጸዋል።
የአምራች ዘርፉ የሀገርን ኢኮኖሚ በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና ቢኖረውም፤ አሁንም ድረስ የፋይናንስ አቅርቦት እና የቴክኖሎጂ (የመሳሪያ) እጥረት እንደ ትልቅ ማነቆ እንደሆነ ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ያሉ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም 66.67% ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ምክትል ከንቲባው ይህንን የማምረት አቅም አጠቃቀም በ2022 ዓ.ም ወደ 85% ለማሳደግ ታቅዶ እየተከናወነ ሲሆን ይህ ግብ እንዲሳካ ግን የፋይናንስ፣ የማሽነሪ፣ የቦታ እና የመሠረተ ልማት አቅርቦት ችግሮችን በቅንጅት መፈታት እንዳለባቸው ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ አሳስበዋል።
በመጨረሻም አምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት ለመጨመር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ውይይት የተደረገ ሲሆን በፖሊሲ መመለስ ያለባቸው ተቋማት በሚመልሷቸው እና ባንኮች ከኢንዱስትሪ ቢሮ ጋር ተቀራርበው በሚሰሩበት ጉዳይ ላይ መግባባት ተደርሷል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments