ቢሮው የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ክፍለ ከተሞ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

ቢሮው የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ክፍለ ከተሞችና ዳይሬክቶሬቶች እውቅናና ሽልማት አበረከተ።

ቢሮው ባለፉት ስድስት ወራት ተጨባጭና ውጤታማ የስራ አፈጻጸም መመዝገቡን በእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ውይይት ወቅት የፋሲሊቴሽንና የካይዘን ትግበራ ዘርፍ ኃላፊ ኤፍሬም ግዛው (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ኤፍሬም ግዛው (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ በሀገር ደረጃ ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል የአምራች ዘርፍ አንዱ ሲሆን አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉና በገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ባለፉት ስድስት ወራት በአሰራር፣ በአደረጃጀትና በክህሎት ማጎልበት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።

በተጨማሪም ቢሮው በቀጣይ ዕቅድን በመከለስና ግንዛቤ በመፍጠር ወደ ተግባር መግባት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ፣ በሪፎርም ስራዎች ላይ ወጥ የሆነ ግንዛቤ መፍጠር፣ ተናባቢ የሆነ የክትትልና ድጋፍ ስራን ማጠናከርና የአቅም ግንባታ አፈጻጸምን ማጠናከር በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

በቢሮው የተካሄደው አፈጻጸም ግምገማ ላይ ተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ውይይት አደረጉ፣ ቢሮውም አበይትና ቁልፍ ተግባራትን በተናባቢ ዕቅድ በማካተት፣ ግንዛቤ በመፍጠር ወደ ስራ መግባት፣ ወጥነት ያለው አሰራር በመዘርጋት፣ አደረጃጀትን በማስተካከልና ስራን መሠረት ያደረገ ስልጠና በመስጠት የተሻለ የስራ አፈጻጸም ተመዝግቧል።

በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ  ስድስት ወራት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ክፍለ ከተሞች እና የቢሮው ዳይሬክቶሬቶች  እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በ2018 ግማሽ በጀት ዓመት ከ1 እስከ 3 የወጡ   ክፍለ ከተሞች

1ኛ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ፣

2ኛ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት

3ኛ  ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ  ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ፣

ከ1 እስከ 3 የወጡ   ዳይሬክቶሬቶች

1ኛ. የስነ ምግባርና ጸረ–ሙስና ዳይሬክቶሬት፣ 

2ኛ.የኢንዱስትሪ ልማት ካይዘን ሽግግር ዳይሬክቶሬት

3ኛ.የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ዳይሬክቶሬት


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments