ቢሮው ከማእከል እስከ ክፍለ ከተማ ላሉ የዘርፍ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ ።
ስልጠናው በኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ፣ በህግ ማእቀፎች፣ በአሰራር ማኑዋሎች፣ በቢሮው የ2017 አፈጻጸምና በ2018 ዋና ዋና ግቦች እና በሪፎርም ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
ስልጠናውን ያስጀመሩት የልደታ ክፍለ ከተማ የኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ዱላ ስልጠናው በ2017 በጀት ዓመት የነበሩ ክፍተቶችን በማስተካከል በበጀት ዓመቱ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት በትኩረት ለመስራት አቅም ይሆናል ብለዋል።
የአምራች ኢንዱስትሪዎች ልማት የአገልግሎትና ድጋፍ ማእቀፍ መመሪያ ቁጥር 166/2017 በቢሮው የኢንዱስትሪ ልማት ካይዘን ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገናናው ተስፋሁን አቅርበዋል።
በመመሪያው ላይ የመስሪያ ቦታ ተጠቃሚ አምራች ኢንዱስትሪዎች ልየታና ምልመላ መስፈርቶች፣ የካፒታል እቃ እና የፋይናንስ ብድር አቀርቦት፣ የገበያ ትስስርና ፕሮሞሽን፣ የዘርፍ ማህበራት አደረጃጀት፣ የእድገት ደረጃ አወሳሰንና ሽግግር ድጋፎችን ለመስጠት መከተል ያለበትን መስፈርቶች በዝርዝር አቅርበዋል።
መመሪያዎቹን አውቆ ድጋፍ ማድረግ ከተጠያቂነት ለመዳንና የቢሮውን ግብ ለማሳካት ሚናው ከፍ ያለ ነው ሲሉ አቶ ገናናው ተናግረዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments