የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ያስለማው የአምራች ኢንዱስትሪ የተቀናጀ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት (IIMS) በይፋ ተመረቀ፡፡
ቢሮው ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ያስለማውን የአምራች ኢንዱስትሪ የተቀናጀ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት (Integrated Industry Management Information System) በዛሬው እለት በድምቀት አስመርቋል።
በእለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተከበሩ ጃንጥራር አባይ ከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርን ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው በዛሬው እለት የተመረቀው ቴክኖሎጂ አንድ ማሳያ ነው ብለዋል።
የለማው ቴክኖሎጂ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ምዝገባ እስከ ምርት ምዝገባ ያለውን መረጃ የያዘ ሲሆን አምራች ኢንዱስትሪዎች በኦንላይ መረጃ እንዲያገኙ ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንደሚያግዝ ገልጸው ቴክኖሎጂው 12 ዋና እና 31 ንኡስ አገልግሎት መያዙን ጠቁመዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂና ቢሮ ኃላፊ አቶ አወሌ መሀመድ በበኩላቸው የለማው ሲስተም ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ቀልጣፋና ፍትሀዊ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ብለዋል።
በመጨረሻም የለማውን ቴክኖሎጂ የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን ባለድርሻ አካላት እና በየደረጃው ያለው አመራር የለማውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ለአምራች ኢንዱስትሪው ፈጣንና በቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስበዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments