የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ጽ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት " የኢትዮጵያ  ታምርት" ንቅናቄ የማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ።

 

በፕሮግራሙ የአዲስ አበባ ከተማ  ምክትል ከንቲባ እና  የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ  ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ  የክፍለ ከተማው አመራሮች፣ ባለድርሻ አካላት እና በክፍለ ከተማው ውስጥ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ተሳትፈዋል።

የመክፈቻ ንግግር  ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ  ምክትል ከንቲባ እና  የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ  ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ የኢትዮጵያ  ታምርት" ንቅናቄ ለ5ኛ ጊዜ እየተካሄደ እንደሆነ ገልጸው ኢንዱስትሪዎች ገበያን በማረጋጋት፣ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ፣የስራ እድል በመፍጠር እንዲሁም ተኪ ምርት በማምረት ያላቸው ሚና ከፍተኛ  እንደሆነ ገልጸዋል።

መንግስት ልዩ ትኩረት ካደረገባቸው ዘርፎች እንዱ ኢንዱስትሪ እንደሆነ የገለጹት ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ  አምራች  ኢንዱስትሪዎች  ጥራት ያለው ምርት በማምረት ተወዳዳሪ መሆን እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

 አቶ ጃንጥራር አክለውም  ኢንዱስትሪዎች ለሀገር ልማት ያላቸውን  አስተዋጽኦ በመረዳት  በየደረጃው ያለ  አመራር  አምራቾችን መደገፍና ማበረታታት እንደሚገባቸው  አሳስበዋል።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቴውድሮስ ወልደ ሚካኤል በበኩላቸው የኢትዮጵያ  ታምርት" ንቅናቄ አምራቾች የሚገጥማቸውን ችግር በመፍታት ምርታማነታቸውን በማሳደግ ሚናው ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸው የክፍለ ከተማው አስተዳደርም ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

የክፍለ ከተማው ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ  አቶ  የኔው ሞሴ  በበኩላቸው  የኢትዮጵያ  ታምርት ንቅናቄ  አምራቾች የሚገጥማቸውን  ችግር በመፍታት ጥራት ያለው ምርት  እንዲያመርቱ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንዳስቻላቸው ገልጸው በቀጣይም የአምራቾችን ምርታማነት ለማሳደግ ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ  በትኩረት  እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በመጨረሻም በተያዘው ግማሽ በጀት ዓመት ምርት ወደ ውጭ በመላክ ፣ ተኪ ምርት በማምረት  እና ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር  የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው አምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments