የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአገር ውስጥ ምርታማነትን ለማሳደግና የገበያ ትስስርን ለማጠናከር ሚናው የላቀ እንደሆነ ተገለጸ።
የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ የኤግዚቢሽንና ባዛር ፕሮግራም ከየካቲት 13 እስከ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ይከናወናል።
በዚህ ዙሪያ በባዛርና ኤግዚቢሽን ከሚሳተፉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።
የፋሲሊቴሽንና ካይዘን ትግበራ ዘርፍ ኃላፊ ኤፍሬም ግዛው (ዶ/ር) እንደገለጹት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መድረክ ምርት ከመሸጥ ባለፈ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ውጤቶች ለህብረተሰቡና ለሸማቾች የሚተዋወቁበት እንዲሁም በአምራቾች መካከል የግብዓት ትስስር የሚፈጠርበት ሰፊ አውድ እንዳለው አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በዋናነት አንዱ አምራች ለሌላው ግብዓት የሚሆንበትን ሁኔታ በማመቻቸት አምረቾች እንዲቀራረቡ በማድረግ ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ዶ/ር ኤፍሬም ገልጸዋል።
ይህ ዝግጅት አምራቾች እርስ በርስ ልምድና ዕውቀት እንዲለዋወጡ ከማስቻሉም ባለፈ፤ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና የተለያዩ ተቋማት የአገር ውስጥ ምርቶችን ደረጃ ተመልክተው አስፈላጊውን የፖሊሲ ድጋፍና የማበረታቻ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥሩ መሆኑን ዶ/ር ኤፍሬም ተናግረዋል።
መንግስት ትኩረት ከሰጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ዘርፎች አንዱ የሆነው አምራች ኢንዱስትሪ የደረሰበትን የእድገት ደረጃ የሚያሳይበት ይህ ዝግጅት፤ በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ቀጥተኛ ክትትል የሚመራ ሲሆን ከቀደሙት ዓመታት በተሻለና በላቀ ዝግጅት እንዲከናወንም አቅጣጫ ተቀምጦለት እየተሰራ እንደሚገኝ ዶ/ር ኤፍሬም ገልጸዋል።v
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments