አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ ሁሉም ባለድርሻ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት አለባቸው ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ

የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ከየካቲት 14 ቀን 2018 ዓ. ም ጀምሮ  ከተማ አቀፍ #የኢትዮጵያ_ታምርት_ንቅናቄ ባዛርና ኤግዚቢሽን  በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እያካሄደ  ነው።

በዛሬው እለትም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ  ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላት እና የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች በተገኙበት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች  ላይ  የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩ መክፈቻ ንግግር  ያደረጉት  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር  አባይ  ውይይቱ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚታዩትን የፋይናንስ፣ የመሥሪያ ቦታና የመሠረተ-ልማት አቅርቦት ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ጃንጥራር አክለውም፣ መንግሥት ለአምራች ዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ማነቆዎችን ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ በተለይም የማሽነሪ ሊዝ ድጋፍ፣ የብድር አቅርቦትና የሥራ ማስፋፊያ መሬት ጥያቄዎች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ምላሽ እንደሚያገኙ አስታውቀዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የባለድርሻ አካላት ተወካዮች በበኩላቸው  በአምራች ኢንዱስትሪውና በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል የነበረውን ቅንጅት በማጠናከር የአምራቾችን ጥያቄዎች  ለመመለስና ለዘርፉ ዕድገት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪዎ ባለቤቶች በበኩላቸው  መንግሥት እያደረገላቸው ያለው  ዘርፈ-ብዙ ድጋፍ  ለምርታማነታቸው  ሚናው የላቀ እንደሆነ  ገልጸው  ተኪ ምርት በማምረት፣ ጥራት ያላቸው ምርቶችን ለውጭ ገበያ በማቅረብና የውጭ ምንዛሬን በማስገኘት ረገድ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ገልጸዋል።

ኤግዚቢሽንና ባዛሩ እስከ መጭው  የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ. ም ድረስ  ይቀጥላል።

 #ኢትዮጵያ_ታምርት_አዲስአበባ_ትበልጽግ


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments