መንግስት ባስቀመጣቸው የስምንት ወር ዋና ዋና ግ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

መንግስት ባስቀመጣቸው የስምንት ወር ዋና ዋና ግቦች የሶስት ወር  ከአስራ አምስት ቀን የአፈጻጻም ሪፖርት  ተገመገመ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ  መንግስት ባስቀመጣቸው የስምንት ወር ዋና ዋና ግቦች ላይ  ባለፉት ሶስት ወር ከአስራ አምስት ቀን በተሰሩ ስራዎች ላይ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

 በውይይቱም በመቀነስ እና የዜሮ  ግብ፣ የአንድ ግብ፣ በእጥፍ  ግብ፣በመቶ ፐርሰንት ግብ፣፣ በፕሮጀክት አፈፃፀም ፣ በገቢ አሰባሰብ  አፈፃፀም፣በስራ  እድል ፈጠራ  እና በሌሎች ግቦች ላይባለፉት ሶስት ወራት  የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት  ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ባለፉት ሶስት ወር  ከ15 ቀን  ኑሮ ውድነትን በማረጋጋት፣  በስራ እድል ፈጠራ፣በከተማ ግብር ፣በገቢ አሰባሰብ፣ እና በሌሎች ስራዎች  ግቦቹን ለማሳካት በክፍለ ከተማው  የተሻለ ስራ እንደተሰራ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር  አባይ ገልጸዋል።

አቶ ጃንጥራር አክለውም  መንግስት የያዛቸውን  ግቦች  ለማሳካት አመራሩ በትኩረት መስራት እንዳለበት ገልጸው የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የምርት አቅርቦትን መጨመር ፣የገበያ መሰተ ልማትን ማቅረብ እና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

 ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰው ተኮር   ተጨባጭ  ስራዎችን ለመስራት  እና ግቦቹን ለማሳካት ሁሉም  በየደረጃው ያለ አመራር  በትኩረት መስራት እንዳለበት ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር  አቅጣጫ አሳስበዋል።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ  ምስክር ነጋሽ (ዶ.ር) በበኩላቸው  ባለፉት ሶስት ወር ከ15 ቀን   የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በክፍለ ከተማው  በርካታ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም ከዚህ በላይ መስራት እንደሚገባ ገልጸው  በቀጣይ ሁሉም አመራር በመቀናጀት የተሻለ ስራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments