የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በአምራች ኢንዱስትሪው...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ያስመዘገበው ተጨባጭ ስኬት እያመጣ መሆኑ ተገለጸ።

‎የቢሮው የኢንዱስትሪ ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጳውሎስ ኩሳ በ5ኛው ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ላይ ኢትዮጵያ የምታሳየው እድገት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገለጹ።

‎ኢትዮጵያ_ታምርት_አዲስ_አበባ_ትበልጽግ"!  በሚል መሪ ቃል የተጀመረው አገራዊ ንቅናቄ በተለይም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ተዳክሞ የነበረውን የአምራች ዘርፍ ለማነቃቃትና አምራቾች የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና እንደተጫወቱ አቶ ጳውሎስ አስረድተዋል።

‎በከተማ ደረጃ የተከናወኑ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም በየዓመቱ እያደገ የመጣ ሲሆን፣ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ የማምረት አቅሙ ከነበረበት 66 በመቶ ወደ 69 በመቶ ከፍ ማለቱ የዘርፉን ጥንካሬ ያሳያል ሲሉ አቶ ጳውሎስ አብራርተዋል።

‎ኃላፊው አክለው አገሪቱ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ምርቶች በመተካት ረገድ ከፍተኛ ውጤት እያመጣች መሆኗን ገልጸዋል።

‎በአሁኑ ወቅት በአገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶችን የመጠቀም አቅማችን 45 በመቶ መድረሱ የተረጋገጠ ነው ያሉት አቶ ጳውሎስ ይህ ስኬት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በማስቀረት ረገድ የጎላ ድርሻ አለው ብለዋል። ከዚህም ባለፈ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች  በአይነትና በመጠን እየጨመሩ መምጣታቸው ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ትልቅ አቅም እየሆነ መምጣቱን ኃላፊው ተናግረዋል።

‎በ2014 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት የተጀመረው የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ችግር የመፍታትና የማነቃቃት ስራ ዛሬ ላይ ተጨባጭ ፍሬዎችን እያፈራ እንደሚገኝ አቶ ጳውሎስ አስረድተዋል።

‎በመጨረሻም አቶ ጳውሎስ ባስተላለፉት መልዕክት፣ አምራች ኢንዱስትሪዎች የጥቂት ባለሀብቶች ብቻ ሳይሆኑ የመላው ኢትዮጵያውያን ሀብት በመሆናቸው በመገንዘብ ሁሉም ዜጋ የአገር ውስጥ ምርትን በመግዛትና በመጠቀም የኢኮኖሚ እድገቱን እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

‎‎#ኢትዮጵያ_ታምርት_አዲስ_አበባ_ትበልጽግ"!


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments