ቢሮው የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ኤግዚቢሽንና...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

ቢሮው የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ኤግዚቢሽንና ባዛር የማጠቃለያ መርሃ-ግብር አካሄደ።

የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ “ኢትዮጵያ ታምርት፤ አዲስ አበባ ትበልፅግ” በሚል መሪ ቃል  ከየካቲት 13 ቀን  ጀምሮ  በደመቀ ሁኔታ ሲካሄድ የቆየው የንቅናቄ ኤግዚቢሽንና ባዛር ዛሬ የማጠቃለያ መርሃ-ግብሩን አካሂዷል።

በመዝጊያ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላት እና የአምራቾች  ተገኝተዋል።

ከየካቲት 13 እስከ 21/2018 ዓ.ም ድረስ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር በቆየው በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ ከ230 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ለጎብኚዎች አስተዋውቀዋል።

እንዲሁም ከሸማቾች ጋር ቀጥተኛ የገበያ ትስስር በመፍጠር ረገድም ሚናው  ከፍተኛ ሲሆን  በተለይም በከተማዋ የሚገኙ አምራቾች ያላቸውን የማምረት አቅምና የጥራት ደረጃ በተግባር ያሳዩበት ሆኖ አልፏል።

በማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ላይ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የመጣውን  ለውጥ  የተመለከተ የውይይት ሰነድ ቀርቧል። 

እንዲሁም ከፍተኛ አፈጻጸም ላሳዩ እና ውጤታማ ተሳትፎ ላደረጉ አምራቾች እና ባለድርሻ አካለት የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷል።

 ይህም አምራቾች በቀጣይ በላቀ ተነሳሽነት ወደ ሥራ እንዲገቡና ለከተማዋ የኢኮኖሚ ዕድገት የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማበረታታት የታለመ ነው።

የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ፣ አምራች ኢንዱስትሪው ለከተማዋ ብልጽግና ያለውን የማይተካ ሚና በመገንዘብ፣ መሰል የገበያ ትስስርና የድጋፍ መድረኮችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመርሃ-ግብሩ ላይ ተመላክቷል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments