ለማዕከል እና ለክፍለ ከተማ ባለሙያዎች  ሲሰጥ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

ለማዕከል እና ለክፍለ ከተማ ባለሙያዎች  ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

የቢሮው የስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት እና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል፤ ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ለማዕከል እና ለክፍለ ከተማ ባለሙያዎች  ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

ስልጠናው በዋናነት በሪፎርም ስራዎች እቅድ ላይ ያተኮረ ሲሆን ባለፈው ስድስት ወራት የነበሩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እና የነበሩ ክፍቶችን ለማረም እና የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ወሳኝ እንደሆነ በቢሮው የስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት እና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል፤ ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት  ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ትልቅሰው ገልጸዋል።።

አቶ ግዛቸው አክለውም  ስልጠናው ለሁሉም ባለሙያዎች የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር ጥራት ያለው አገልግሎት  ከመስጠት በተጨማሪ የተገልጋዮችን የእርካታ ደረጃ ለማሳደግ ወሳኝ እንደሆነ ገልጸዋል።

ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት የተገልጋዩን ፍላጎት ማወቅና መረዳት፣በተገልጋዩ እና በመንግስት መካከል ጠንካራ ግንኙነት መመስረት፣የፈፃሚ አቅም ማሳደግ፣ቃል በተገባው መሰረት ማገልገል እና ፈጠራና ቀጣይነት ያለው መሻሻል መፍጠር ዋና ዋና አስቻይ ጉዳዮች እንደሆኑ አቶ ግዛቸው ገልጸዋል፡፡

የአገልግሎት ስታንዳርድን  በመጠን፣በጊዜ፣በጥራት በመለካት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንደሚገባም ተገልጿል፡፡

በመጨረሻም እንደዚህ አይነት  ስልጠናዎች ስራችንን ይበልጥ በማሳለጥ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ወሳኝ እንደሆነ ገልጸው በቀጣይም የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ሰልጣኞች ገልጸዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments